
መግቢያ
የዛሬውን የትምህርት ክፍላችንን ሌሎች ሶስቱ ወንጌላዊያን በጹሑፋቸው ውስጥ አላካተቱም። ሉቃስ ብቻ ነው በዚህ ክፍል ውስጥ ያካተተው። ዛሬ የምንነጋገርበት ርዕሰ ጉዳይ ዘወትር ለመጸለይ አትታክቱ በሚል ይሆናል። ይህ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ነው። ይሄንን ነገር ከመናገሩ በፊት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሉቃስ ወንጌል 17 መጨረሻ ላይ ስለመምጣቱ ለደቀመዛሙርቱ ከነገራቸው በኃላ ስለ ጸሎት አስፈላጊነትና እንዴት መጸለይ እንደሚገባቸው በምሳሌ ስለመበለቲቱና ሰለ ዓመፀኛው ዳኛ አንስቶ ሲያስተምራቸው እናያለን።
ዘወትር ሳይታክቱ እንዲጸልዩ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረበት ምክንያት ወደ ኢየሩሳሌም እየተጓዙ ስለሆነ፤ ከደቀመዛሙርቱ ጋር የሚኖረው ጊዜ እያጠረ በመምጣቱ፤ ደቀመዛሙርቱን ከእግዚአብሔር አባቱ ጋር ሊያገናኛቸው ፈልጓል። እንዲገናኙ የሚፈልግበት መንገድ አንዱ ሁልጊዜ ሳይታክቱ ዘወትር እንዲጸልዩ እና ከእግዚአብሔር ጋር የተገናኘ ሕይወት እንዲኖራቸው እና እንዲለማመዱ ለማሳሰብ በምሳሌ ይናገራቸዋል።
ስለጸሎት ስናስብ በተለያዩ ጊዜአቶች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እንጸልያለን። አንዳንድ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ዘንድ በምንጸልይባቸው ጉዳዮች ፈጣን መልስ እናገኛለን። አንዳንዴ ይዘገይብናል። ደጋግመን ጸልየን መልስ ስናጣ እግዚአብሔር የሰማን አይመስለንም። በዚህም ምክንያት መታከት እንጀምራለን። በጸሎት ሆነን እግዚአብሔርን አንጠብቅም። እንሰለቻለን። ጌታችን ኢየሱስ ለዚህ አጭርና ግልጽ ትምህርት ይሰጣል። ይሄውም ሁል ጊዜ መጸለይ እንጂ መታከት እንደማይገባን ለእኛም እንድ ደቀማዛሙርቱ ይነግረናል። ኢየሱስ የሚያነሳው ምሳሌ የጸሎት መልሳችን ገና ስላልመጣ ብቻ መጸለይ ማቆም እንደሌለብን የሚያስተምረን ነው።
- ዳኛው፡- እግዚአብሔርን የማይፈራ እና ሰዎችንም የማያፍር በጣም አስቸጋሪ ሰው ነበረ። (ሉቃ 18፡ 2) በዘመኑ አባባል “በጣም ሙሰኛ” የሆነ ሰው ነው፤ ፍርድን በትክክል የማይፈርድ፤ ፊትንና እጅን አይቶ የሚፈርድ፤ መልካም ግብረ ገብነት የሌለው ዳኛ
- መበለት፡ ባል የሞተባቸው፤ አጋዥ የሌላቸው ምናልባትም ልጆችን የሚያስተዳድሩ ይሆናሉ። ዳኛው ባለበት ከተማ ውስጥ የምትኖር አንዲት መበለት ነበረች። እሷም ከባላጋራዋ ጋር በነበራት ጉዳይ ፍትሕ የምትሻ፤ ዳኛው ትክክለኛ ፍርድ እንዲሰጣት ደጋግማ የምትሄድ ነበረች። (ሉቃ 18፡3–4) ይሁን እንጂ ደጋግማ በመሄድ ከዳኛው ፍትህ ብተጠይቅም መልስ አታጋኝም፤ ዳኛው ለጥያቄዋ ምንም ደንታ የማይሰጠው። መበለቲቷ ግን ደጋግማ በመሄድ ፍትህ የምትጠይቅ ነበረ።
- “ይህች መበልት ደጋግማ ለምንድ ነው?” የምትጠይቀው የሚል ጥያቄ ቢነሳ “ አንድ ቀን ፍትሕ አገኛለሁ የሚል “እምነት”” ነበራትና ደጋግማ ትቀርባለች። ትጠይቃለች። ብትከለከልም ተስፋ አልቆረጠችም። መዝሙረኛው ዳዊት መዝሙር 40 ላይ “ቆይቼ እግዚአብሔር ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኽቴንም ሰማኝ።” ይለናል ስለ እግዚአብሔር ፊት መጥናት ሲያነሳ። ጌታችን ስለጸሎት ሲናገር በማቲ 7፡7 ላይ “ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።” ሐዋሪያው ጳውሎስ ደግሞ በሮሜ 12፡12 ላይ ስለጸሎት ሲናገር “ በጸሎት ጽኑ፤” ይላል።
- መበልቲቱ በጽናት እስከ መጨረሻው ቆመች በመጨረሻም ዳኛው እርምጃ እንዲወስድ አደረገች። “ይህች መበለት ስለምታደክመኝ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ።” እስሊል ድረስ(ሉቃ 18፡5)። ይህች መበለት በችግር ወቅት በቁርጠኝነት መቆምን ታስተምረናለች።

(ሉቃስ 18፡6–7)
"ኢየሱስ ክርስቶስ አመጸኛ ዳኛውን እና እግዚአብሔርን በማነጻጸር የሚያሳየን “የጻድቁ እግዚአብሔር ባሕርይ ነው።”
ኢየሱስ በዓመፀኛው ዳኛና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን ልዩነት ሲያሳይ፡
- ዳኛ፡ እግዚአብሔርን የማይፈራ፤ ሰውንም የማያፍር ሲጨቀጨቅ ሰምቶ የመለሰ
- እግዚአብሔር የእኛ አባትና አምላክ፡
ጨካኝ አይደለም፤ እውነተኛ ፈራጅ ዳኛ ነው። እንዲሁ ከፍቅሩ የተነሳ ሰዎች ልማናቸውን በፊቱ ሲያቀርቡ ሰምቶ የሚመልስ ዳኛ ነው። ለድሀ አድዱና ለመበሊቲቱ እንድንፈርድና እንድንሞግት መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል።( ኢሳ 1፡17፤ 23)።
እግዚአብሔር ጻድቅና ፍትሐዊ ነው። ዳዊት “እግዚአብሔር ጽድቅንና ፍትሕን ያደርጋል።” ብሎ በመዝሙር 103፡6 ይናገራል።
የሕዝቡን ጩኸት የሚሰማ አምላክ ነው። መዝሙረኛው በመዝሙር 34፡17 “ጻድቃን ሲጮኹ እግዚአብሔር ይሰማቸዋል።” ይለናል። በመዝ 34፡6 ላይም አሳቡን ይደግመዋል መዝሙረኛው እንዲህ ሲል “ይህ ችግረኛ ጮኸ፥ እግዚአብሔርም ሰማው፥ ከመከራውም ሁሉ አዳነው።” የሚሰቃዩትን ያስባል። ይሁን እንጂ እኛ የምንፈልገው ፈጣን መልስ ነው።
የእግዚአብሔር ጊዜ ከእኛ ጊዜ የተለየ ቢሆንም እርሱ ግን ታማኝ ነው። በራሱ ጊዜና መንገድ የሚመልስ አምላክ ነው። ```ጽዮን በኢሳያስ 49 ፡ 14 እንዳለችውም ብንልም፤ እንደ ዕንባቆም ከእግዚአብሔር ጋር ብንከራከርም (ዕማ 1፡1- 17) ግን ቢዘገይም በእርግጥ እንደሚመጣ አውቀን መታገስ ይግባናል (ዕም 2፡3)። “የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።” (ዕም 3፡16 -17) ማለት ይጠበቅብናል። የጸሎት መልሳችንን በምንጠባበቅበት ጊዜ በፊቱ በባሕሪው፣ በጥበቡና በፊትሑ መታመን ያስፈለጋል። ባይመለስልንም እንኳን እግዚአብሔር እውነተኛ ዳኛ ነው።
- “ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?”(ሉቃ 18፡8) ብሎ ኢየሱስ ጥያቄ ያቀርባል። ምክንያቱ በመከራ ውስጥ በእምነት መጽናት ቀላል ጉዳይ ስላልሆነ። በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥም እግዚአብሔር አደርጋለሁ ብሎ ሲዘገይባቸው ተስፋ በመቁረጥ የራሳችውን ውሳኔ በመወሰን በመንገዳቸው የሄዱ ሰዎችን እናገኛለን። ለምሳሌ አብርሃም ማየት ይቻላል። አብርሃም እግዚአብሔር እንደሚባርከው በዘፍጥረት 12፡1- 3 ተናገረው። አብርሃም ትንሽ ቆይቶ ተፈተነ። “ወራሽ የለኝም” ሲል እግዚአብሔር ግንን “እርሱ አይወርስህም ነገር ግን ከጉልበትህ የሚወጣው እርሱ ይወርስሃል ጠብቅ” ብሎ መለሰለት በዘፍ 15፡1–6:: አብርሃም ግን መጠበቅ አቅቶት የሚስቱን ምክር ሰምቶ አገልጋዩ አጋር ጋር እነደገባ ሁላችንም የምናወቀው ጉዳይ ነው። በእምነት መጽናት አልቻለም።
- በመከራ ውስጥ ለእርዳታ በመለመን መጽናትን ብቻ ሳይሆን በእምነትን መጽናትን የሚያሳይ ነጥብ ነው። ለጸሎት አለመታከት፤ እግዚአብሔር እስኪመለስ ድረስ እንጽና፤ በእምነት መጠብቅ፤ በእግዚአብሔር በመታመን መጠበቅ ያስፈልጋል። ለዚህ ነው ያዕቆብ “በፈተና የሚጸና ብፅህ ነው። ” የሚለን በያዕቆብ 1፡12 ላይ።

ማጠቃለያ
የዛሬው ትምህርታችን በመከራ ውስጥ ሆነን መጸለያችንን፤ በእግዚአብሔር መታመናችንን አናቁም። የክርስቶስን ዳግመኛ መምጣት በተስፋ መጠበቃችንን እንድንቀጠል ኢየሱስ እንዲህ ይላል። “እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ” (ሉቃ 18፡7)። በ2ኛ ነገስት 3፡17 ላይ ኤልሳ እንዲህ አለ “ነፋስ አታዩም፥ ዝናብም አታዩም፥ ይህ ሸለቆ ግን ውኃ ይሞላል፤ እናንተም ከብቶቻችሁም እንስሶቻችሁም ትጠጣላችሁ።” እኛ በምንፈልገው ጊዜ ሳይሆን በራሱ ጊዜ እና መንገድ፤ እኛ በማማቀው ጊዜና ሁኔታ ለጸሎታችን መልስ ይሰጠናልና በጽናት በእምነት እንቁም። እንጠብቀው። አሜን!
መልእክተ እሑድ፡ ነሐሴ 15 | 2019 ዓ.ም. (October 25, 2026) የጽሑፍ ዝግጅት፡ ደሳለኝ ዳንኤል