ወደ ዋና ይዘት ሂድ

ስብከቶች

በስብከቶቻችን ሰምቶ ወይም ተመልክቶ ለእምነት ማደግ።

ዘወትር ለመጸለይ አትታክቱመልእክተ እሑድ

ዘወትር ለመጸለይ አትታክቱ

ቄስ ዶ/ር አብዲ ታደሰጥቅምት 25, 2026

# መግቢያ የዛሬውን የትምህርት ክፍላችንን ሌሎች ሶስቱ ወንጌላዊያን በጹሑፋቸው ውስጥ አላካተቱም። ሉቃስ ብቻ ነው በዚህ ክፍል ውስጥ ያካተተው። ዛሬ የምንነጋገርበት ርዕሰ ጉዳይ ዘወትር ለመጸለይ አትታክቱ በሚል ይሆናል። ይህ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ነው። ይሄንን ነገር ከመናገሩ በፊት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሉቃስ ወንጌል 17 መጨረሻ ላይ ስለመምጣቱ ለደቀመዛሙርቱ ከነገራቸው በኃላ ስለ ጸሎት አስፈላጊነትና እንዴት መጸለይ እንደሚገባቸው በምሳሌ ስለመበለቲቱና ሰለ ዓመፀኛው ዳኛ አንስቶ ሲያስተምራቸው እናያለን። ዘወትር ሳይታክቱ እንዲጸልዩ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረበት ምክንያት ወደ ኢየሩሳሌም እየተጓዙ ስለሆነ፤ ከደቀመዛሙርቱ ጋር የሚኖረው ጊዜ እያጠረ በመምጣቱ፤ ደቀመዛሙርቱን ከእግዚአብሔር አባቱ ጋር ሊያገናኛቸው ፈልጓል። እንዲገናኙ የሚፈልግበት መንገድ አንዱ ሁልጊዜ ሳይታክቱ ዘወትር እንዲጸልዩ እና ከእግዚአብሔር ጋር የተገናኘ ሕይወት እንዲኖራቸው እና እንዲለማመዱ ለማሳሰብ በምሳሌ ይናገራቸዋል። ስለጸሎት ስናስብ በተለያዩ ጊዜአቶች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እንጸልያለን። አንዳንድ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ዘንድ በምንጸልይባቸው ጉዳዮች ፈጣን መልስ እናገኛለን። አንዳንዴ ይዘገይብናል። ደጋግመን ጸልየን መልስ ስናጣ እግዚአብሔር የሰማን አይመስለንም። በዚህም ምክንያት መታከት እንጀምራለን። በጸሎት ሆነን እግዚአብሔርን አንጠብቅም። እንሰለቻለን። ጌታችን ኢየሱስ ለዚህ አጭርና ግልጽ ትምህርት ይሰጣል። ይሄውም ሁል ጊዜ መጸለይ እንጂ መታከት እንደማይገባን ለእኛም እንድ ደቀማዛሙርቱ ይነግረናል። ኢየሱስ የሚያነሳው ምሳሌ የጸሎት መልሳችን ገና ስላልመጣ ብቻ መጸለይ ማቆም እንደሌለብን የሚያስተምረን ነው። - **ዳኛው**፡- እግዚአብሔርን የማይፈራ እና ሰዎችንም የማያፍር በጣም አስቸጋሪ ሰው ነበረ። (ሉቃ 18፡ 2) በዘመኑ አባባል “በጣም ሙሰኛ” የሆነ ሰው ነው፤ ፍርድን በትክክል የማይፈርድ፤ ፊትንና እጅን አይቶ የሚፈርድ፤ መልካም ግብረ ገብነት የሌለው ዳኛ - **መበለት**፡ ባል የሞተባቸው፤ አጋዥ የሌላቸው ምናልባትም ልጆችን የሚያስተዳድሩ ይሆናሉ። ዳኛው ባለበት ከተማ ውስጥ የምትኖር አንዲት መበለት ነበረች። እሷም ከባላጋራዋ ጋር በነበራት ጉዳይ ፍትሕ የምትሻ፤ ዳኛው ትክክለኛ ፍርድ እንዲሰጣት ደጋግማ የምትሄድ ነበረች። (ሉቃ 18፡3–4) ይሁን እንጂ ደጋግማ በመሄድ ከዳኛው ፍትህ ብተጠይቅም መልስ አታጋኝም፤ ዳኛው ለጥያቄዋ ምንም ደንታ የማይሰጠው። መበለቲቷ ግን ደጋግማ በመሄድ ፍትህ የምትጠይቅ ነበረ። - “ይህች መበልት ደጋግማ ለምንድ ነው?” የምትጠይቀው የሚል ጥያቄ ቢነሳ “ **አንድ ቀን ፍትሕ አገኛለሁ የሚል “እምነት”**” ነበራትና ደጋግማ ትቀርባለች። ትጠይቃለች። ብትከለከልም ተስፋ አልቆረጠችም። መዝሙረኛው ዳዊት መዝሙር 40 ላይ “ቆይቼ እግዚአብሔር ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኽቴንም ሰማኝ።” ይለናል ስለ እግዚአብሔር ፊት መጥናት ሲያነሳ። ጌታችን ስለጸሎት ሲናገር በማቲ 7፡7 ላይ “ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።” ሐዋሪያው ጳውሎስ ደግሞ በሮሜ 12፡12 ላይ ስለጸሎት ሲናገር “ በጸሎት ጽኑ፤” ይላል። - መበልቲቱ በጽናት እስከ መጨረሻው ቆመች በመጨረሻም ዳኛው እርምጃ እንዲወስድ አደረገች። “ይህች መበለት ስለምታደክመኝ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ።” እስሊል ድረስ(ሉቃ 18፡5)። ይህች መበለት በችግር ወቅት በቁርጠኝነት መቆምን ታስተምረናለች። ![IMGL0558.jpg](https://wadmin.aaecmy.org/uploads/IMGL_0558_3a5ee556c7.jpg) (ሉቃስ 18፡6–7) >"ኢየሱስ ክርስቶስ አመጸኛ ዳኛውን እና እግዚአብሔርን በማነጻጸር የሚያሳየን “የጻድቁ እግዚአብሔር ባሕርይ ነው።” ኢየሱስ በዓመፀኛው ዳኛና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን ልዩነት ሲያሳይ፡ - **ዳኛ፡** እግዚአብሔርን የማይፈራ፤ ሰውንም የማያፍር ሲጨቀጨቅ ሰምቶ የመለሰ - **እግዚአብሔር የእኛ አባትና አምላክ፡** ጨካኝ አይደለም፤ እውነተኛ ፈራጅ ዳኛ ነው። እንዲሁ ከፍቅሩ የተነሳ ሰዎች ልማናቸውን በፊቱ ሲያቀርቡ ሰምቶ የሚመልስ ዳኛ ነው። ለድሀ አድዱና ለመበሊቲቱ እንድንፈርድና እንድንሞግት መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል።( ኢሳ 1፡17፤ 23)። እግዚአብሔር ጻድቅና ፍትሐዊ ነው። ዳዊት “እግዚአብሔር ጽድቅንና ፍትሕን ያደርጋል።” ብሎ በመዝሙር 103፡6 ይናገራል። የሕዝቡን ጩኸት የሚሰማ አምላክ ነው። መዝሙረኛው በመዝሙር 34፡17 “ጻድቃን ሲጮኹ እግዚአብሔር ይሰማቸዋል።” ይለናል። በመዝ 34፡6 ላይም አሳቡን ይደግመዋል መዝሙረኛው እንዲህ ሲል “ይህ ችግረኛ ጮኸ፥ እግዚአብሔርም ሰማው፥ ከመከራውም ሁሉ አዳነው።” የሚሰቃዩትን ያስባል። ይሁን እንጂ እኛ የምንፈልገው ፈጣን መልስ ነው። የእግዚአብሔር ጊዜ ከእኛ ጊዜ የተለየ ቢሆንም እርሱ ግን ታማኝ ነው። በራሱ ጊዜና መንገድ የሚመልስ አምላክ ነው። ```ጽዮን በኢሳያስ 49 ፡ 14 እንዳለችውም ብንልም፤ እንደ ዕንባቆም ከእግዚአብሔር ጋር ብንከራከርም (ዕማ 1፡1- 17) ግን ቢዘገይም በእርግጥ እንደሚመጣ አውቀን መታገስ ይግባናል (ዕም 2፡3)። “የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።” (ዕም 3፡16 -17) ማለት ይጠበቅብናል። የጸሎት መልሳችንን በምንጠባበቅበት ጊዜ በፊቱ በባሕሪው፣ በጥበቡና በፊትሑ መታመን ያስፈለጋል። ባይመለስልንም እንኳን እግዚአብሔር እውነተኛ ዳኛ ነው። - “ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?”(ሉቃ 18፡8) ብሎ ኢየሱስ ጥያቄ ያቀርባል። ምክንያቱ በመከራ ውስጥ በእምነት መጽናት ቀላል ጉዳይ ስላልሆነ። በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥም እግዚአብሔር አደርጋለሁ ብሎ ሲዘገይባቸው ተስፋ በመቁረጥ የራሳችውን ውሳኔ በመወሰን በመንገዳቸው የሄዱ ሰዎችን እናገኛለን። ለምሳሌ አብርሃም ማየት ይቻላል። አብርሃም እግዚአብሔር እንደሚባርከው በዘፍጥረት 12፡1- 3 ተናገረው። አብርሃም ትንሽ ቆይቶ ተፈተነ። “ወራሽ የለኝም” ሲል እግዚአብሔር ግንን “እርሱ አይወርስህም ነገር ግን ከጉልበትህ የሚወጣው እርሱ ይወርስሃል ጠብቅ” ብሎ መለሰለት በዘፍ 15፡1–6:: አብርሃም ግን መጠበቅ አቅቶት የሚስቱን ምክር ሰምቶ አገልጋዩ አጋር ጋር እነደገባ ሁላችንም የምናወቀው ጉዳይ ነው። በእምነት መጽናት አልቻለም። - በመከራ ውስጥ ለእርዳታ በመለመን መጽናትን ብቻ ሳይሆን በእምነትን መጽናትን የሚያሳይ ነጥብ ነው። ለጸሎት አለመታከት፤ እግዚአብሔር እስኪመለስ ድረስ እንጽና፤ በእምነት መጠብቅ፤ በእግዚአብሔር በመታመን መጠበቅ ያስፈልጋል። ለዚህ ነው ያዕቆብ “በፈተና የሚጸና ብፅህ ነው። ” የሚለን በያዕቆብ 1፡12 ላይ። ![IMGL0575.jpg](https://wadmin.aaecmy.org/uploads/IMGL_0575_9dd011c287.jpg) # ማጠቃለያ የዛሬው ትምህርታችን በመከራ ውስጥ ሆነን መጸለያችንን፤ በእግዚአብሔር መታመናችንን አናቁም። የክርስቶስን ዳግመኛ መምጣት በተስፋ መጠበቃችንን እንድንቀጠል ኢየሱስ እንዲህ ይላል። “እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ” (ሉቃ 18፡7)። በ2ኛ ነገስት 3፡17 ላይ ኤልሳ እንዲህ አለ “ነፋስ አታዩም፥ ዝናብም አታዩም፥ ይህ ሸለቆ ግን ውኃ ይሞላል፤ እናንተም ከብቶቻችሁም እንስሶቻችሁም ትጠጣላችሁ።” እኛ በምንፈልገው ጊዜ ሳይሆን በራሱ ጊዜ እና መንገድ፤ እኛ በማማቀው ጊዜና ሁኔታ ለጸሎታችን መልስ ይሰጠናልና በጽናት በእምነት እንቁም። እንጠብቀው። አሜን! መልእክተ እሑድ፡ ነሐሴ 15 | 2019 ዓ.ም. (October 25, 2026) የጽሑፍ ዝግጅት፡ ደሳለኝ ዳንኤል

የዘላለም ሊቀ-ካህን መልእክተ እሑድ

የዘላለም ሊቀ-ካህን

ቄስ ዶ/ር ድንቁ ለሜሳሐምሌ 10, 2026

>²³እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤ ²⁴እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ ²⁵ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል። ²⁶ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞችም የተለየ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባልና፤ ²⁷እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና። ²⁸ሕጉ ድካም ያላቸውን ሰዎች ሊቀ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፤ ከሕግ በኋላ የመጣ የመሐላው ቃል ግን ለዘላለም ፍጹም የሆነውን ልጅ ይሾማል። ዕብ. 7፥23–28 **መግቢያ** በዚህ ክፍል እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ልጅ ለማዳን በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የመሠረተውን አዲሱን ኪዳን እንመለከታለን። በዚህም ኪዳን የሚያገለግለውን ታላቁንና ዘላለማዊ የሆነውን ሊቀ-ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንመለከታለን። በመጀመሪያ እንደምናውቀው በኃጢአት የወደቀው የሰውን ልጅ ለማዳን ሲል እግዚአብሔር አምላክ እራሱ ወደ አዳም መጣ። ይህንንም ያደረገው ከራሱ ጋር ለማስታረቅ ነበር። ከዚያም እግዚአብሔር አምላክ ለእስራኤል ሕዝብ ሕጉን ሲሰጥ ለኃጢአት ማስተሰርያ ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉትን የተለያዩ የእንስሳት የመሥዋዕት ሥርዓትን አብሮ ሰጥቶ ነበር። በዚህም በቀደመው ኪዳን ካህናቱ በየጊዜውና በዕየለቱ የተለያዩ መሥዋዕቶችን በማቅረብ፣ በዓመት አንድ ጊዜ ደግሞ ሊቀ-ካህኑ ለእራሱና ለሕዝቡ የሚሆን የኃጢአት ስርየት መሥዋዕትን በማቅረብ በመገናኛ ድንኳን ውስጥ ውስንነት በነበረው በቀደመው ኪዳን ያገለግሉ ነበር ዘሌ. 9፥8–15። **ይህ ሁሉ ግን የሕዝቡንም ሆነ የካህናቱን ሕሊና ሊያነፃና ሊያድን የማይችል የሥጋ ስርዓት ብቻ ነበር።** በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር አምላክ ይህን የቀደመውን ኪዳን ሽሮ አንድያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን እውነተኛ የመሥዋዕት በግ እንዲሆን ፈቅዶ፣ መጥቶም ፍጹም አምላክና ሰው ሆኖ ሞቶ አዲሱን ኪዳን ከፈተ። ይህ አዲሱ ኪዳን እግዚአብሔር በቀጠረው ጊዜ ሆኖአል፤ ከእግዚአብሔርም ጋር ማስታረቅ ችሏል። በዚህም ክፍል እንደምናየው ይህ አዲሱ ኪዳን በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ የሆነልን ፡- - ስለ እኛ ሊማልድ ዘወትር የሚኖር (ቁ. 25) - ለዘላለም የሚኖር እና የማይለወጥ ክህነት ያለው ሊቀ-ካህን (ቁ. 24) - በእርሱ በኩል የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድን የሚችል (ቁ. 25) - ፍጹም የሆነ የመሥዋዕት በግ፣ ቅዱስና ተንኮል የሌለበት (ቁ. 26) - ዕለት ዕለት መሥዋዕት ማቅረብ የማያስፈልገው፣ አንድ ጊዜ የፈጸመ (ቁ. 27) መሆኑን ማየት እንችላለን፡፡ በዚህ አዲሱ ኪዳን በኢየሱስ ክርስቶስ በእርሱ በኩል የመጣነውን ፈጽሞ ካዳነን በኋላ ከእኛ የሚጠብቀው ነገር ደግሞ አለው፡፡ እርሱም፡- ለሌሎች ይህንን ታላቅ የማዳን ሥራ በማስታወቅ እነርሱ ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲታረቁ ማድረግ ነው፡፡ _የጽሑፍ ዝግጅት፡_ **ብሌን ሙሉጌታ**

Video available